Open menu
Adama Science and Technology University Signs MoU with Adama Hospital Medical College
ASTU Signs Memorandum of Understanding with Gambella University
Adama Science and Technology University Signs Memorandum of Understanding with Hormuud University
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎቹን አስመረቀ
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎቹን አስመረቀ
Adama Science and Technology University Hosts the 7th Annual Job Expo 2026
Adama Science and Technology University Signs MoU with Ethiopian Nuclear Energy Commission
ASTU Conducts Training on HCERES Academic Program Accreditation Standards for Academic Staff
ASTU Conducts Training on HCERES Academic Program Accreditation Standards for Academic Staff
Adama Science and Technology University Signs MoU with Entrepreneurship Development Institute
Adama Science and Technology University Signs MoU with Entrepreneurship Development Institute
Adama Science and Technology University Partners with Ministry of Transport and Logistics and Debre Berhan University
Adama Science and Technology University (ASTU) cooperated with China- Africa Innovation Cooperation
Adama Science and Technology University and the Ethiopian Aviation University discuss areas of collaboration
ASTU Delegation Visits Hubei University of Technology in China to Establish Strategic Partnership
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች (alumni) ካርኒቫል ተከበረ
ወደ ራስገዝ ዩኒቨርሲቲነት ሽግግር እያደረገ ባለበት በአሁኑ ወቅት የመጀመሪያውን የቀድሞ ተማሪዎች ካርኒቫል በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር የሚገኙ በርካታ የቀድሞ ተመራቂዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።፡፡
Adama Science and Technology University (ASTU) organized a validation workshop
Adama Science and Technology University (ASTU) convened a successful validation workshop for the research project entitled "Technology Need Assessment and Strategic Roadmap for the ICT, Trade, Transport and Environment sectors of Oromia Regional State" on May 2, 2025, at the Dire International Hotel in Adama, Ethiopia.
Adama Science and Technology University Signs MoU with Adama Hospital Medical College

4th

የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለ32ኛ ዙር ያስተማራቸውን 1387 ተማሪዎች ሰኔ 13 2018 ዓ. ም በአ.ሳ.ቴ.ዩ ሁለገብ አዳራሽ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፣የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት አስመርቋል ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንደተናገሩት ዓለም በፈጣን የሳይንስና ቴክኖሎጂ እድገት፣ በዲጂታል ኢኮኖሚ መስፋፋትና በአካባቢ ጥበቃ ተግዳሮቶች ምክንያት ከፍተኛ

የለውጥ ግፊት ውስጥ እንደምትገኝ በመጠቆም ሀገራት ዘላቂ ልማትንና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን ለማረጋገጥ ለዕውቀትና ለፈጠራ ትኩረት መስጠት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ለዝግጅቱ ታዳሚዎች አስገንዝበዋል።
በመቀጠልም ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ኢትዮጵያ አሁን የሚያስፈልጋት የቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች ብቻ ሳይሆኑ የሀገራችንንና የዓለምን ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች፣ ባለራዕይ ተመራማሪዎችና ስራ ፈጣሪዎች ጭምር መሆኑንም አስገንዝበዋል።
ተመራቂዎች ራሳቸውን ሥራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆኑ የስራ ዕድል ፈጣሪዎች አድርገው እንዲመለከቱና የመማራቸው እውነተኛ ዋጋ በማኅበረሰቡ ህይወት ላይ በሚያመጡት አዎንታዊ ተፅዕኖ እንደሚለካ በመገንዘብ በቀጣይ በሚሰማሩበት የሥራና የሕይወት መስክ ሁሉ ስኬትና መልካም እድል እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል።
በተመሳሳይ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር እና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸዉ ተመራቂ ተማሪዎች የሀገራቸዉን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን" እዉን ለማድረግ የበኩላቸዉን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሚኒስርሩ አያይዘዉም የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ምሩቃን በትላልቅ ኢንዱስትሪዎችና ኩባንያዎች ዉስጥ በመሰማራት እያበረከቱ ላለዉ አስተዋፅዖ እውቅና ሰጥተዋል፡፡
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ለሚ ጉታ በበኩላቸዉ ከ2018 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች (1387) ዉስጥ 324ቱ ወይም 23.3% ሴቶች መሆናቸዉንና ዩኒቨርሲቲዉ በአለዉ ልዩ ካሪኩለም ተጠቃሚ ከሆኑት 9 ዱዋል ሜጀር/ማይነር ተማሪዎች መካከል 3ቱ ሴቶች መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ሴት ተማሪዎቻችን በትምህርታቸዉ አመርቂ ዉጤት ማምጣት ብቻ ሳይሆን ተምሳሌታዊ ስራን እየሰሩ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
ይኸውም በዩኒቨርሲቲዉ የኤሌክትሪካል ፓወር ኤንድ ኮንትሮል ኢንጅነሪንግ (Electrical Power and Control Engineering) ተመራቂ ተማሪና የዋንጫ ተሸላሚ የሆነችዉ ሩት አባተ ከወሰደቻቸው 60 ኮርሶች መካከል 47ቱን 'A+' እንዲሁም የቀሩትን 13 ኮርሶች 'A' በማምጣት ሙሉ 4.00 (አራት ነጥብ) ያመጣችዉንና የፋርማሲ ዱዋል ሜጀር/ ማይነር ተመራቂ የሆነችዉን ተሊሌ ደሳለኝን መጥቀስ እንደ ማሳያ መዉሰድ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ለሚ አያይዘዉም ለተመራቂ ተማሪዎች እዉቀታቸዉንና ክኅሎታቸውን ለህዝቦች መቀራረብ የሚያገለግሉ ድልድዮችን ለመገንባት እንዲጠቀሙበት አደራ ብለዋል፡፡
ተመራቂዎቹ በተለያዩ የትምህርት መርሃ ግብሮች በመጀመርያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ እና በሶስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በመደበኛና በተከታታይ ትምህርት ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው።
የተማሪዎች ምርጥ የምርምር ፕሮጀክት ዉጤቶች በዝግጅቱ ታዳሚዎች የተጎበኙ ሲሆን በዚህ ስራቸው የተሻለ ዉጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Media Gallery

  • fenote1.jpg
  • fenote2.jpg
  • fenote3.jpg
  • fenote4.jpg
  • gc1.jpg
  • gc2.jpg
  • gc3.jpg
  • gc4.jpg
  • gc5.jpg
  • gc6.jpg
  • gc7.jpg
  • gc8.jpg
  • gc9.jpg
  • gc10.jpg
  • gc11.jpg
  • gc12.jpg
  • gc13.jpg
  • pg1.jpg
  • space1.jpg
  • space2.jpg
  • space3.jpg
  • sriel1.jpg
  • sriel2.jpg
  • State-Minster.jpg
  • State-Minster1.jpg-.jpg
  • summit1.jpg
  • summit2.jpg
  • _K8A6031.JPG
  • _K8A6104.JPG
  • _K8A6127.JPG

ASTU Campuse Map

maps1

Contact us

International Relations and Corporate Communications
Office: +251 -22-211-3961,  Email: irccd@astu.edu.et
P.O.Box: 1888 Adama, Ethiopia
Office of Registrar  
Office: +251 -221-100001,  Email: sar@astu.edu.et
P.O.Box: 1888 Adama, Ethiopia


   © 2024  Adama Science and Technology University